ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት እያጠናከረች ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ፣ በልማት እና በባንክ ዘርፎች ከሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያላትን የፋይናንስና የኢኮኖሚ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እያጠናከረች ነው።

የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በታይላንድ ባንኮክ ተካሄዷል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና የግል ዘርፍ ተወካዮች ጋር ስትራቴጂካዊ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርጓል።

ልዑኩ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ቴክኖሎጂ (Visa)፣ ከጣልያኑ የልማት ባንክ (Cassa Depositi e Prestiti - CDP)፣ እንዲሁም ከባንክ ኦፍ አሜሪካ (Bank of America) ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይቷል።


 

ውይይቶቹም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ፣ የዲጂታል ፋይናንስ መሰረተ ልማትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የልማት ፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት እና ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ባንኮች አውታር ጋር ማስተሳሰር በሚችለባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም