ቀጥታ፡

የመደመር መንግሥት የሃይማኖት ተቋማት ለአብሮነት ያላቸውን ሚና በመረዳት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግሥት የሀይማኖት ተቋማት ሰላምን ለማፅናት እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ያላቸውን ጉልህ ሚና አጠናክሮ ለመቀጠል በትኩረት ይሰራል ሲሉ በሰላም ሚኒስቴር የግጭት አፈታት እና ሰላም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ገለፁ።

የሰላም ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በመተባበር የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።


 

በዚህ ወቅት ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የሃይማኖት ተቋማት ከእምነት አስተምህሯቸው ባሻገር ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ይቅርታን እና አብሮነትን በማስተማር ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የመደመር መንግሥት የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ እና አብሮነት ያላቸውን ሚና በመረዳት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የመደመር መንግሥት የሃይማኖት ተቋማት ሰላምን ለማፅናት እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ያላቸውን ጉልህ ሚና አጠናክሮ ለመቀጠል በትኩረት ይሰራል ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው የሀገር ሰላም የሚፀናው በሁሉም ዜጋ የጋራ ተሳትፎ ነው ብለዋል።


 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሸረፋ ሌጋሶ በበኩላቸው፤ ሊገጥሙ በሚችሉ የሰላም ስጋቶች ዙሪያ ምክክር፣ውይይት እና መግባባት በመፍጠር ችግርን በራስ አቅም የመፍታት ባህል ማዳበር ያስፈልጋል ብለዋል።

ከዚህ አንፃር የዛሬው መድረክ የክልሉን ሰላም ለማጠናከር ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም