ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ አጋርነታቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ አጋርነታቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ኢኮኖሚን ጨምሮ የሁለትዮሽ አጋርነታቸውን የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በታይላንድ ባንኮክ ተካሄዷል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ከዓመታዊው ስብሰባ ጎን ለጎን፣ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት መሥሪያ ቤት የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ኤሪክ ሜየር ጋር ውይይት አድርጓል።
የሁለትዮሽ ውይይቱ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማስቀጠልና ለማፋጠን የሚያስችል የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍን ከፍ ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በተለይም በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት በኩል ሊደረጉ የሚችሉ የድጋፍ አማራጮች ላይ ያተኮረ ነው።
ምክትል ረዳት ሚኒስትር ኤሪክ ሜየር ኢትዮጵያ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችን ለመተግበር እያሳየች ያለችውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
አሜሪካ ገንቢ የሆነ የሁለትዮሽ አጋርነት እንዲኖር በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ሁለቱ ወገኖች የጋራ የልማት ግቦችን ለማሳካትና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማጠናከር መደበኛ እና ገንቢ ውይይቶችን አጠናክረው ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።