ድል የናፈቀው ቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን ለማግኘት ከኮቨንተሪ ሲቲ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
ድል የናፈቀው ቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን ለማግኘት ከኮቨንተሪ ሲቲ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።
ምሽት አራት ሰዓት ላይ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከኮቨንተሪ ሲቲ በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ባለሜዳው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሶስት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።
አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ በስድስት ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል ቀንቶታል።
ሁለቱ ክለቦች በሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ13ኛ ጊዜ ነው።
ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 12 ጨዋታዎች ቶተንሃም ሆትስፐርስ ስድስቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። ኮቨንተሪ ሲቲ ሶስቱን ሲያሸንፍ በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
ቶተንሃም በ12ቱ ጨዋታዎች ላይ 21 ግቦችን ሲያስቆጥር ኮቨንተሪ 17 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ የተገናኙት እ.አ.አ በ2001 ነው። በወቅቱ ቶተንሃም ሆትስፐርስ 2 ለ 0 አሸንፏል።
ሁለቱ ክለቦች ከ25 ዓመታት በኋላ ዳግም በሊጉ ይገናኛሉ።
ኮቨንተሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱ የሚታወስ ነው።
በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ከ310 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያወጣው ቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል።
አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ በድል ጉዞው ለመቀጠል ይፋለማል።
የ43 ዓመቱ አንዲ ማድሊ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።