አርሰናል ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት አርሰናል ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኖኒ ማዱዌኬ በ80ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ18 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
የወቅቱ ሻምፒዮን ከሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኖቲንግሃም ፎረስት በአምስት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ብራያን ምቤሞ ለዩናይትድ፣ ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን ለሊድስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ሊድስ ዩናይትድ በ10 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ብራይተን ክሪስታል ፓላስን 5 ለ 0፣ ቦርንማውዝ ሰንደርላንድን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ኮቨንተሪ ሲቲ ነገ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።