በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲዳማ ቡና ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲዳማ ቡና ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2019 (ኢዜአ):- በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያደረገው ሲዳማ ቡና በሱዳኑ አል ሂላል ኦምዱርማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሐመድ ዩሱፍ እና የሲዳማ ቡናው ደስታ ደሙ በራሱ ላይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ጥቅምት 15 2019 ዓ.ም በሩዋንዳ ይካሄዳል።
ሲዳማ ቡና ወደ ምድብ ድልድሉ ለመግባት ውጤቱን መቀልበስ ይኖርበታል።
በያሬድ ገመቹ የሚሰለጥነው ሲዳማ ቡና በአህጉራዊ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ይታወቃል።