ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ የሊጉ መሪ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ የሊጉ መሪ ሆነ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 8/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቻልን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሄኖክ ኤርሚያስ በ47ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ሄኖክ በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ብዛት ሁለት አድርሷል።
ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስድስት ነጥብ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በበኩሉ በሶስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአብዩ ኤርሳሞ በተደረገው ጨዋታ ጋናዊው ፕሪንስ ባዱ ለሀዲያ ሆሳዕና፣ መሳይ ሰለሞን ለወላይታ ድቻ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሀዲያ ሆሳዕና በአንድ ነጥብ 14ኛ፣ ወላይታ ድቻ በሁለት ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ ሁለተኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።