የአምስተርዳም ማራቶን በኢትዮጵያ አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአምስተርዳም ማራቶን በኢትዮጵያ አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 8/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ለሚ ብርሃኑ በወንዶች እና ቡዜ ድሪባ በሴቶች የ2026ቱን (የቲሲኤስ አምስተርዳም) ማራቶን ውድድር አሸንፈዋል።
ለሚ ብርሃኑ የወንዶችን ውድድር በ2 ሰዓት ከ3 ደቂቃና 33 ሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ ሲወጣ፣ ቡዜ ድሪባ የሴቶችን ውድድር በ2 ሰዓት 16 ደቂቃና 10 ሰከንድ በመግባት አጠናቃለች።
አትሌት ቡዜ ድሪባ የውድድሩን የሴቶች ኮርስ ሪከርድም ሰብራለች።
በዚህም ኢትዮጵያውያኑ በሁለቱም ጾታ የአመስተርዳም ማራቶን ውድድርን በበላይነት አጠናቀዋል።