ቀጥታ፡

የነዋሪዎቻችንን ኑሮና አኗኗር ለማሻሻል በትጋት እየሠራን ነው-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የበጎነት መኖሪያ ሕንፃ ለአቅመ ደካሞችና ለሀገር ባለውለታዎች በደስታ አስረክበናል።

ከዚህ በፊት ለመኖር በማይመች ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ወገኖቻችን ዛሬ በተሟላ መሠረተ ልማት የታገዘ ምቹ መኖሪያ ቤት በማግኘታቸው የኑሮ ጫናቸው ቀንሷል፤ ልባቸውም በደስታና በተስፋ ተሞልቷል።

ለእኛ የቤት ልማት ማለት ሕንፃ መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ክብር ማስጠበቅ፣ የኑሮ ጥራትን ማሻሻልና የተሻለ ነገ መገንባት ነው።


 

የከተማችንን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመቅረፍና ለነዋሪዎቻችን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹና ክብር የተሞላበት ኑሮ ለመፍጠር ጥረታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ከዚህ ቀደም በደሳሳና ለመኖር በማይመች ቤት ውስጥ ስትኖሩ የነበራችሁ ወገኖቻችን፣ ዛሬ ወደ አዲሱ መኖሪያችሁ በመግባታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! አዲሱ ቤታችሁ የደስታ፣ የሰላም፣ የክብርና የተስፋ መኖሪያ ይሁንላችሁ!


 

“በጋራ እንሠራለን፤ የነዋሪዎቻችንን ኑሮ እናሻሽላለን!” በሚል ጥሪ ስናቀርብላችሁ፣ በጎ ምላሽ በመስጠት ከጎናችን የቆማችሁና ለዚህ በጎ ተግባር አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ የሪል እስቴት አልሚዎችን በተጠቃሚዎች ስም ከልብ እናመሰግናለን። እንዲህ ያለው አጋርነት የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል የተሻለች ከተማ እንድንገነባ ያግዘናል።

በጋራ በመሥራት የተሻለ ኑሮና የተሻለች አዲስ አበባ እንገነባለን!

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም