ቀጥታ፡

በአፋር ክልል አዳዲስና ተጓትተው የነበሩ የውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቷል

 ሰመራ፣ ጥቅምት 8/2019 (ኢዜአ)፡- በአፋር  ክልል አዳዲስና በተለያዩ ምክንያቶች ተጓትተው የነበሩ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ሻሚ እንደገለጹት፣የህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ጥያቄ በተደራጀ አግባብ ለመመለስ በተለይም ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የሚሰራው ስራ ውጤት እያስገኘ ነው ። 

ለዚህም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ፍጥነትና በጀት ከመገንባት ጎን ለጎን፣ የቆዩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ወደ ስራ የማስገባትና ነባር ተቋማትን የማጠናከር ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

የክልሉን የውሃ ሽፋን ከ67 በመቶ ወደ 72 በመቶ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ለአብነትም በሃደለኤላ ወረዳ የነባር የውሃ ጉድጓዶችን አገልግሎት የማሳደግና ሌሎች 16 የውሃ ፕሮጀክቶችን በቶሎ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ 315 የውሃ ተቋማትን በፀሃይ ሀይል እንዲሰሩ በማድረግ አገልግሎቱን  ዘላቂ የማድረግና ለጄኔሬተር  ነዳጅና ለትራንስፖርት ይወጣ የነበረውን ተጨማሪ ወጪ ማስቀረት መቻሉንም አስረድተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም