ቀጥታ፡

አትሌት ታምራት ቶላ የቤጂንግ ማራቶንን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 8/2019 (ኢዜአ)፦ አትሌት ታምራት ቶላ የቤጂንግ ማራቶን ውድድርን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፏል።

በሴቶች ምድብ በተካሄደው ውድድር ደግም አትሌት አንቺንአሉ ደሴ ማሸነፍ ችላለች።

የኢትዮጵያ አትሌቶች በበላይነት ባጠናቀቁት በዚህ ውድድር የ2026 የቤጂንግ ማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ በበላይነት አጠናቋል።

አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ የቀድሞውን የውድድሩን ክብረ ወሰን በአራት ደቂቃዎች በማሻሻል ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።


 

በሴቶች ምድብ በተካሄደው ውድድር ደግሞ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ ውድድሯን በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በማጠናቀቅ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የቤጂንግ ማራቶን አሸናፊ መሆን ችላለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም