ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2019 (ኢዜአ)፦ ዳንኤል ጸሐዬ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ያሬድ ቶሌራ እና መስዑድ መሐመድ ደግሞ በረዳት አሰልጣኝነት የሚሰሩ መሆኑን ገልጿል።
ብሔራዊ ቡድኑ ከ23 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ጥቅምት ወር መጨረሻ እና ህዳር ወር መጀመርያ ላይ ሞሮኮን ይገጥማል።
የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ እ.አ.አ በ2027 በግብጽ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።