ቀጥታ፡

ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2019(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሩንዲያዊው አልፍሬድ ኩሪንዚዛ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል መድን መሪ ሆኗል።

ጌታነህ ከበደ በ62ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ ባሳረፈው ግብ ሃዋሳ ከተማ አቻ ሆኗል።

የኢትዮጵያ መድን የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ዋንጫ ቱት እና አብዱል ጋንዩ በቀይ ካርድ ተሰናብተዋል።

በሊጉ የመጀመሪያ ነጥቡን ያገኘው ሃዋሳ ከተማ 14ተኛ ደረጃን ይዟል።

ኢትዮጵያ መድን በአራት ነጥብ የሊጉ መሪ ሆኗል።

ዛሬ በተደረገው የደርቢ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም