መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት በጀግንነት እያስከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት በጀግንነት እያስከበረ ነው
ሰቆጣ፤ ጥቅምት 7/2019 (ኢዜአ)፦ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት በጀግንነት እያስከበረ መሆኑ ተገለጸ።
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ዛሬ ተካሂዷል።
የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጌትነት እሸቱ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት በጀግንነት እያስከበረ ነው።
መከላከያ ሰራዊት የሃገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እየፈጸመ ባለው ጀግንነት የአባቶቹን አደራ በተግባር እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ህብረተሰቡም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን አጋርነትና ደጀንነት ለመግለጽ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ማካሄዱን አመልክተዋል ።
በብልፅግና ፓርቲ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዳግም ባይነሳኝ በበኩላቸው በመከላከያ ሰራዊት ብርቱ ክንድ የሀገር አንድነትና ሉአላዊነት ጸንቶ ለትውልድ ይተላለፋል ብለዋል።
መከላከያ ሰራዊት እየፈጸመ ባለው ጀግንነት የሀገርን እድገት ለማፋጠን ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል።
የሃገር መከላከያ ሰራዊት የህብረ ብሄራዊና የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን ጠቁመው የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት በማስከበር ጀግንነቱን እየተወጣ መሆኑን አመልክተዋል።
የህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎችም የሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት አርማ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንን እንደግፋለን!"፣ ለድል የተወለደው ሰራዊታችን አለኝታችን ነው!" የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።