ቀጥታ፡

የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ አመራሮች በትጋትና በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል 

ቦንጋ ፤ ጥቅምት 7/2019 (ኢዜአ)፦ ለህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በየደረጃው ያለን አመራሮች በትጋትና በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፍቅሬ አማን ገለጹ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል "ማንሰራራት ለክልላችን ከፍታ በሚል" መሪ ሀሳብ የአመራሮች የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።


 

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፍቅሬ አማን፤ የተሰጠን የህዝብ አደራ አቅዶ ወደ ስራ በመግባትና አጠናቆ ለአገልግሎት በማብቃት ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ ነው ብለዋል።

ከህዝቡ የተነሱ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በመመለስ የክልሉን ከፍታና ማንሰራራት እውን ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም ለህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በየደረጃው ያለን አመራሮች በትጋትና በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ለዚህም ጠንካራ የአሰራር ስርዓት በመገንባት በተደመረ አቅም ለክልሉ ብሎም ለሀገር እድገትና ብልጽግና መስራት ይኖርብናል ብለዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም