ቀጥታ፡

የሀገር መከታ ለሆነው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የተሰጠ ክብር

ጎንደር፣ ሰቆጣ፣ ገንዳ ውሃ ፤ ጥቅምት 7/2019 (ኢዜአ)፦ የሀገር መከታ ለሆነው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የተሰጠ ክብር።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በጀግንነቱ፣ በታማኝነቱ፣ በቁርጠኝነቱና ተልእኮ በመፈፀም ብቃቱ በጉልህ የሚነሳ ጠንካራ ሰራዊት መሆኑ ይታወቃል።


 

የሀገሩን ክብርና ሉአላዊነት እንዲሁም ዳር ድንበር ከማስከበር ባለፈ በአህጉራዊ የሰላም ማስከበር ተልእኮ ቀዳሚ መሆኑም እንዲሁ።

የሀገር ሉአላዊነት የመጨረሻ መከታ የሆነው ሰራዊት የሀገርን ዳር ድንበር በመጠበቅና ለሕዝብ ደህንነት በጀግንነት መስዋእትነት በመክፈል ሀገርን በጽናት ያቆመ ሃይል ነው።


 

ለዚሁ ጀግና ሰራዊት ክብርና ምስጋና የሚሰጥ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

የሀገር መከታና የሕዝብ አገልጋይ ለሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ምስጋና እና ተገቢውን ክብር መስጠት ተገቢ ነው።

በመሆኑም በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሰራዊቱን የሀገር ውለታ፣ የጀግንነት መገለጫዎቹንና የጽናት ምልክትነቱን የሚያንፀባርቁ መልእከቶችን በማንገብ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ይገኛል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም