በገንዳ ውሀ ከተማ መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በገንዳ ውሀ ከተማ መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ገንዳ ውሀ፤ ጥቅምት 7/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሀ ከተማ መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ከማለዳ ጀምሮ ወደ አደባባይ የወጡት የከተማው እና የአካባቢው ነዋሪዎች መከላከያ ሠራዊታችን ብሔራዊ አርማችን ነው፣ ባንዳ ለሆዱ፤ መከላከያ ሠራዊታችን ለሕዝባችን ክብር እና አንድነት፣ መከላከያ ሰራዊታችን የህብረ-ብሄራዊነታችን ማሳያ አርማችን ነው የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች እያስተላለፉ ይገኛሉ።