ቀጥታ፡

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሽንፈት አስተናገደ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2019 (ኢዜአ)፦ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ አል አህሊ ትሪፖሊ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 4 ለ 0 ረትቷል።

ጨዋታው ትናንት ማምሻውን በትሪፖሊ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ተካሄዷል።

የመልሱ ጨዋታ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ምድብ ድልድሉ ለመግባት በመልሱ ጨዋታ ውጤቱን መቀልበስ ይኖርበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም