ቀጥታ፡

የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በላቀ ተነሳሽነትና ሌት ተቀን እየተሰራ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2019 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የህዝቡን ተጠቃሚነት በተግባር የማረጋገጥ ስራዎች  በላቀ ተነሳሽነትና ሌት ተቀን እየተሰራ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪና የካቢኔ አባለት፤ በከተማው አሁን ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት፣ የተቋማት ማዕከል፣ የመንገድና የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ለህዝቡ የገባነውን ቃል ወደ ተግባር ለመቀየርና የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።

በተለይም ፕሮጀክቶቹ በፍጥነትና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እየተሰሩ መሆኑን ነው የተናገሩት።

 የመሰረተ ልማትና ሌሎች ስራዎች የበርካታ ዜጎች የልማት ጥያቄዎችን እየመለሱ ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም