አዳማ ከተማ እና ሸገር አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አዳማ ከተማ እና ሸገር አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2019 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሓ ግብር አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሄዷል።
ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማና ሸገር ከተማ በተመሳሳይ አራት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሸገር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ዛሬ በተደረጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ሀላባ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።