ቀጥታ፡

አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2019 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀላባ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዮናታን ኃይሉ በ48ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

አዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ የመጀመሪያ ድሉን በማስመዝገብ በአራት ነጥብ የሊጉ መሪ ሆኗል።

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በሶስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

በሶስተኛ ሳምንት ሀላባ ከተማ ከፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማ ከወላይታ ድቻ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም