ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2019 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ነገሌ አርሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ነጥቡን ያገኘ ሲሆን 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በተከታታይ ጨዋታዎች አቻ የወጣው ነገሌ አርሲ በሁለት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሸገር ከተማ እና ነገሌ አርሲ ከኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።