በትግራይ ክልል ለተዋቀረው የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ተልዕኮዎችን በበላይነት የሚመሩ ዋና አስፈጻሚዎች እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ ተሹመዋል - ኢዜአ አማርኛ
በትግራይ ክልል ለተዋቀረው የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ተልዕኮዎችን በበላይነት የሚመሩ ዋና አስፈጻሚዎች እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ ተሹመዋል
በትግራይ ክልል ለተዋቀረው የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ተልዕኮዎችን በበላይነት የሚመሩ ዋና አስፈጻሚዎች እና የመቐለ ከተማ ከንቲባ መሾማቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በዚህም መሠረት የባለአደራ አስተዳደሩን የሥራ ዘርፎች የሚመሩት ዋና አስፈጻሚዎች፦
አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ፦ የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ፤
ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ ወ/ሥላሴ፦ የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ፤
ብሪጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሔር በየነ ኃይሉ፦ የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ፤
አቶ ረዳኢ ኃለፎም ወ/ሥላሴ፦ የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤
ዶክተር ሽሻይ አማረ፦ የመቐለ ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።
የተሾሙት አመራሮች በክልሉ የሰላም፣ የመልሶ ግንባታ፣ የመዋቅር ዝርጋታ እና የሕዝብ አገልግሎት መስጠት ዋና ዋና ባለአደራነቶችን በበላይነት የሚያስተባብሩ ይሆናል።