ቀጥታ፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ  ከአል አህሊ ትሪፖሊ ጋር ያደርጋል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2019 (ኢዜአ):- በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ ጋር ጨዋታውን ያከናውናል።

ጨዋታው ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ በትሪፖሊ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይካሄዳል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያው ዙር ቅድመ ማጣሪያ የሱዳኑን ሂላል አል ሳሂል በመለያ ምት አሸንፎ ወደ ሁለተኛው ዙር መቀላቀሉ የሚታወስ ነው። 

ተጋጣሚው አል አህሊ ትሪፖሊ የዛንዚባሩን ኬምኬምን በድምር ውጤት 7 ለ 0 መርታቱ አይዘነጋም።

በግርማ  ታደሰ የሚሰለጥነው   ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ዝግጅቱን አከናውኗል።

ወልዋሎ በአህጉራዊ መድረክ ሲሳተፍ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን የኢትዮጵያ ዋንጫ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ነው።

ተጋጣሚው አል አህሊ ትሪፖሊ በሊቢያ ከሚገኙ ጠንካራ ክለቦች መካከል የሚጠቀስ ነው።

ከዚህ ቀደም በካፍ ሻምፒዮንስ ሩብ ፍጻሜ ደርሶ ያውቃል።

የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታቸውን ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በትሪፖሊ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ ወደ ምድብ ድልድሉ ይገባል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም