ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራርና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራርና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አፀደቀ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራርና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አፅድቋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ በእጩዎች የአመራረጥ ሂደት ከመንግስት ተጠሪ እና ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገበት መሆኑን ገልፀው ብዝሐነትን፣ ብቃትን፣ የሥራ ልምድን፣ በምክር ቤቱ መቀመጫ ያላቸውን የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ታሳቢ ያደረገ እንዲሁም አዲስ እና ነባር አባላትን ያካተተ ለማድረግ ጥረት መደረጉን አንስተዋል።
በዚህም መሰረት፡-
ቀነአ ያደታ (ዶ/ር)፡- የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አቶ ታርጃት ደቦል፡- የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
አቶ መለሰ መና፡- የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
እሱባለው መብራት(ዶ/ር)፡- የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ፡- የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አቶ ጫላ ለሚ፡- የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
አቶ ሰለሞን ላሌ፡- የንግድ፣ ባህልና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አቶ ጣሂር መሀመድ፡- የንግድ፣ ባህልና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፡- የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ወ/ሮ ወላይቴ ቢቶ፡- የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ፡- የብሔራዊ ስትራቴጂ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ወይዘሮ ዝናሽ ፀጋዬ ፡- የብሔራዊ ስትራቴጂ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)፡- የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ፈትሒ ማሕዲ (ዶ/ር)፡- የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
ወይዘሮ የሺሀሳብ ፀጋው፡- የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር)፡- የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
አቶ አለማየሁ እጅጉ፡- የከተማ መሰረተ ልማት እና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር)፡- የከተማ መሰረተ ልማት እና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
አብርሃም አለማየሁ (ዶ/ር)፡- የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ወይዘሮ አራሬ ሞሲሳ፡- የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
አቶ ንጋቱ ወልዴ፡- የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ወይዘሮ ነፊሳ አልማህዲ፡- የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
ወይዘሮ መሰረት ኃይሌ፡- የጤና፣ ማህበራዊ ልማት እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ወይዘሮ ጀሚላ ሲምቢሮ፡- የጤና፣ ማህበራዊ ልማት እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ
ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፡- የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ወይዘሮ ዘሃራ ሰምሬ፡- የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል።
ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራርና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ፤ ውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 4/2019 አድርጎ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።