ባሕር ዳር የከተማ ውበትን ከመደመር መንግሥት የሥልጣኔ ግብ ጋር አስተሳስራ የዘመናዊት ኢትዮጵያን አዲስ ገጽታ እያንፀባረቀች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ባሕር ዳር የከተማ ውበትን ከመደመር መንግሥት የሥልጣኔ ግብ ጋር አስተሳስራ የዘመናዊት ኢትዮጵያን አዲስ ገጽታ እያንፀባረቀች ነው
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ባሕር ዳር የከተማ ውበትን ከመደመር መንግሥት የሥልጣኔ ግብ ጋር አስተሳስራ የዘመናዊት ኢትዮጵያን አዲስ ገጽታ እያንፀባረቀች ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ የክልሉን ፕሬዝደንት ጽ/ቤት እና ቤተመንግስት ግንባታ አስጀምረዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጣና እና ዓባይ በሚታዩበት የጣና ማዕዘን ላይ የሚገነባው ግንባታ ላይ በቦታ መረጣ እና በተሻለ ዲዛይን እንዲገነባ ሐሳብ የሰጡን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አብርክቷቸው ልዩ በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የመደመር መንግሥት የሥራ ከባቢን ከማሻሻልና ደረጃቸውን የጠበቁ ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ርዕይን ማዕከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት እና ቤተመንግስቱ ከክልሉ እሴቶችና መለያ ባህሪያት በመነሳት በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የተነደፈ ሲሆን፣ ዘመናዊነትን ከሀገር በቀል እሳቤ ጋር ያጣመረ ነውም ብለዋል።
የመንግሥት ተቋማትን ማዘመን ለተሻለ አስተዳደርና ለሕዝብ የተሻለ አገልግሎት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉም ገልጸዋል።