የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦችን መርምሮ አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦችን መርምሮ አጸደቀ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ የውሳኔ ሀሳቦችን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሂዷል።
ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።
በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብንም እንዲሁ መርምሮ አጽድቋል።
በተጨማሪም የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራር እና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል።