ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የግማሽ ፍጻሜ ተጋጣሚውን አውቋል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ በ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ በግማሽ ፍጻሜው ከዩጋንዳ ጋር ትጫወታለች።

በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ ሁለት በአራት ነጥብ ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።

ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ ሁለት አንደኛ ሆኖ ካጠናቀቀው የዩጋንዳ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር ለፍጻሜ ለማለፍ ይፋለማል።

ሁለቱ ሀገራት በምድብ ሁለት ትናንት ባደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ መለያየታቸው ይታወቃል።

በማጣሪያ ውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫው ይሳተፋሉ።

17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም