የመደመር መንግስት የገባውን ቃል በተግባር በማከናወን የህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
የመደመር መንግስት የገባውን ቃል በተግባር በማከናወን የህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል
ሐረር ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግስት የገባውን ቃል ተግባር ላይ በማዋል የህዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ
በሐረሪ ክልል የመንግስትና የፓርቲ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት፤ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዘርፍ አበረታች ተግባራትን ማከናወን ተችሏል።
መድረኩ የተዘጋጀው የህዝብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የታቀዱ የመንግስትና የፓርቲ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸምን በመገምገም ለቀጣይ ስራዎች ራስን ማዘጋጀት እንደሆነም አክለዋል።
የመደመር መንግስት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዘገብና አገርን በማሻገር የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት በማጎልበት ላይ ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል።
አመራሩ ለህዝብ የገባውን ቃል ተግባራዊ በማድረግ ሃላፊነቱን መወጣት ይገባል ያሉት አቶ ኦርዲን በዚህም የታዩ ክፍተቶችን በማረም ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ላይ በቅንጅት የሚሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ የክልሉ የመንግስትና የፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።