ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለግማሽ ፍጻሜ አለፈ 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦  በ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ተጠባቂ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ ጋር አቻ ተለያየች።

ማምሻውን በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ዘሚካኤል ምንያህል በ71ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያን መሪ አድርጓል።

ዘሚካኤል በውድድሩ ላይ ሁለተኛ ግቡን አስቆጥሯል።

አርኖልድ ካዬምባ በ78ኛው ደቂቃ ዩጋንዳን አቻ አድርጓል። 

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ምርጥ ሁለተኛ ሆና ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።

ኢትዮጵያ ምርጥ ሁለተኛ የሆነችው በምድብ ሶስት በተመሳሳይ አራት ነጥብ ያላትን ታንዛንያን በግብ ክፍያ በመብለጧ ምክንያት ነው።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ሶስት የግብ ክፍያ፣ የታንዛንያ አቻው  ሁለት ግብ ክፍያ አላቸው።
 
የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።  

የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።

በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ።

17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም