ምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ1ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ.ም ያካሂዳል፡፡
ምክር ቤቱ በነገ መደበኛ ስብሰባው በህገ- መንግስቱ አንቀጽ 55/19/ እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 152 መሰረት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 4/1/ (መ) እና አንቀጽ 5/4/(መ) መሰረት የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራር እና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡