ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ዴንማርክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን በገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ሱኔ ክሮግስትሩፕ ፈርመዋል።


 

በተደረገው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ያሏትን ቅድመ አጀንዳዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅና ለማሳየት የሚያስችላትን የገንዘብ ድጋፍ ዴንማርክ እንደምታቀርብ ተመላክቷል።

ይህ አዲስ ስምምነት ዴንማርክ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሁነቶች ላይ ስታደርግ የቆየችውን ንቁ ተሳትፎ መሰረት በማድረግ የተፈጸመ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ዘላቂ የወደፊት ወዳጅነትና አጋርነት የበለጠ እንደሚያጠናክርም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም