ቀጥታ፡

በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ሁለተኛ ዙር ድጋፍ እየተጓጓዘ ነው

አዳማ ፤ ጥቅምት 04//2019 (ኢዜአ) ፦ በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ሁለተኛ ዙር ድጋፍ እየተጓጓዘ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በዛሬው እለት ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማእከላዊ መጋዘን ሰብአዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ስፍራው ተንቀሳቀሰዋል።

ክልሉ በራሱ አቅም ምላሽ ለመስጠት ርብርብ እያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንም የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል።


 

በዚሁ መሰረትም ከአዳማ ማእከላዊ መጋዘን በአፋር ክልል የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወገኖች ሁለተኛ ዙር ድጋፍ በማጓጓዝ ላይ ይገኛል።

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ በማጠናከር ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በራስ አቅም ምላሽ የመስጠት ጥረቱ የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል።



በመሆኑም በአፋር ክልል የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሹ ወገኖች እየተላከ ያለው ሰብአዊ ድጋፍ በአግባቡ ተደራሽ እንዲሆን የሚደረግ መሆኑን ኮሚሽኑ አመላክቷል።

የመጀመሪያው ዙር የሰብአዊ ድጋፍ ከቀናት በፊት በተመሳሳይ ወደ ክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተጓጓዘ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም