ቀጥታ፡

ስፖርቲንግ ሊዝበን እና ሳባህ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ማምሻውን ተጀምሯል።

በቦላሬት-ዴሌሊስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስፖርቲንግ ሊዝበን ሌንስን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ሉዊስ ሱዋሬዝ በ22ኛው እና ኢሳ ዱምቢያ በ74ኛው ደቂቃ ግቦቹን  አስቆጥረዋል።

የፖርቹጋሉ ክለብ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ በስድስት ነጥብ የሊግ እርከን ውድድሩ መሪ ሆኗል።

የፈረንሳዩ ሌንስ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በሌላኛው መርሃ ግብር ሳባህ ስላቪያ ፕራግን 2 ለ 0 ረትቷል።

በባኩ ኦሊምፒክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ካሂም ፓሪስ በ49ኛው እና ጆይ-ላንስ ሚኬልስ በ88ኛው ደቂቃ ኳስን ከመረብ አገናኝተዋል።

በሻምፒዮንስ ሊጉ የመጀመሪያ ተሳትፎውን እያደረገ የሚገኘው የአዘርባጃኑ ሳባህ የመጀመሪያ ታሪካዊ ድሉን አስመዘግቧል።

በአንጻሩ የቼክ ሪፐብሊኩ ስላቪያ ፕራግ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም