የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ላይ ማሻሻያ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ላይ ማሻሻያ ተደረገ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 15 2019 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የ2019 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጥቅምት 8 እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ተገልጾ ነበር።
ይሁንና የውድድሩን መጀመሪያ ቀን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ጥቅምት 15 2019 ዓ.ም በደርሶ መልስ ፎርማት እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ አመልክቷል።