ቀጥታ፡

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር)ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

አልጋ ወራሹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬትን፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣይነት ያለው እድገት እና ብልጽግናንም ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም