ኮቨንተሪ ሲቲ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ኮቨንተሪ ሲቲ ከወራጅ ቀጠና የወጣበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኮቨንተሪ ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን 4 ለ 1 ረትቷል።
ትናንት ማምሻውን በኮቨንተሪ ቢውሊዲንግ ሶሳይቲ አሬና በተካሄደው ጨዋታ ሲዲኪ ቼሪፍ፣ ኤሊስ ሲምስ፣ ስቴፈን ሙፉኒ እና ጃክ ሩዶኒ (ፍጹም ቅጣት ምት) የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ስቬን ቦትማን ለኒውካስትል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው ኒውካስትል ብልጫ ወስዶ ቢጫወትም ኮቨንተሪ ሲቲ የግብ እድሎችን በሚገባ በመጠቀም የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ በስድስት ነጥብ ደረጃውን ከ19ኛ ወደ 14ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኒውካስትል ዩናይትድ በስምንት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታውን ተከትሎ ስድስተኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።