የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የብሩንዲ አቻውን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የብሩንዲ አቻውን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2 /2018 (ኢዜአ)፦ በ17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ ብሩንዲን 3 ለ 0 ረትቷል።
ማምሻውን በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘሚካኤል ምንያህል፣ አክረም አብዱሰላም እና አብዲሳ ጉተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ የማለፍ እድሉን አስፍቷል።
ብሔራዊ ቡድኑን የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከነገ በስቲያ ከዩጋንዳ ጋር ያከናውናል።
በምድቡ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የብሩንዲ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከማጣሪያው ተሰናብቷል።
ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ከምድቡ አንደኛ መውጣት ወይም ከሶስቱ ምድቦች ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።
የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።
በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ።
17ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 16 ሀገራት ይሳተፋሉ።