የመደመር መንግስት የተለማቸው የልማት ዕቅዶች የህዝቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ናቸው - ኢዜአ አማርኛ
የመደመር መንግስት የተለማቸው የልማት ዕቅዶች የህዝቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ናቸው
አሶሳ፤ ጥቅምት 2//2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግስት በቀጣይ ዓመታት ለማከናወን የተለማቸው የልማት ዕቅዶች ህዝቡን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉና ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ናቸው ሲሉ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ትልቅ ሀገር፤ትልቅ ህዝብ፤ታላቅ ርዕይ
ነዋሪዎቹ እንደገለፁት፤ የመደመር መንግሥት በሚቀጥሉት ዓመታት ለማከናወን ያቀዳቸው ግዙፍ የልማት ግቦችና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ናቸው።
የልማት ዕቅዶቹ በሚቀጥሉት ዓመታት ውስጥ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩ ጠንካራ እምነት እንዳላቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ አስራት ወልደአማኑኤል፤ የመደመር መንግሥት ያቀዳቸው ግቦች ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉና በጠንካራ አንድነት ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
የመደመር መንግሥት በቀጣዮቹ ዓመታት ለማከናወን ያቀዳቸው ግዙፍ የልማት ግቦች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና በተግባር የሚያረጋግጡና ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ እንደሚሆኑም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ኢብራሂም አዙቤር በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት በምርጫ የህዝብ ይሁንታን ያገኘ መንግሥት በመሆኑ በሚሰራቸው የልማት ሥራዎች ጠንካራ የህዝብ ንቅናቄን መፍጠር ይችላል ብለዋል።
የመደመር መንግሥት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሁሉም ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ በተግባር ያሳየ ነው ያሉት ደግሞ ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ጉደታ ነጋሳ ናቸው።
መንግሥት በቀጣይ ዓመታት ለመተግባር የተለማቸውን የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያረጋግጡ ግዙፍ የልማት ተግባራትን ወደ ተግባር መቀየር እንዳለበት እና ህብረተሰቡም ከመንግሥት ጎን በመሆን የልማቱ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ መሆን እንዳለበትም አመልክተዋል።