19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ተከበረ
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ተከብሯል።
የሰንደቅ አላማ ቀኑ የተከበረው “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
በቀኑ አከባበር ላይ ዲፕሎማቶች፣ የኤምባሲ ሰራተኞች እና የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።
በየኤምባሲዎቹ ሰንደቅ ዓላማውን የመስቀል ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስከበርና ልማቷን ለማፋጠን እያደረጉት ያለውን ሀገራዊ ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።
የሰንደቅ አላማ ቀን የሀገርን ክብር ለመጠበቅና ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ የማጠናከር ቃል ኪዳን የታደሰበት ሁነት መሆኑ ተመላክቷል።