ቀጥታ፡

ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መገለጫና በአንድነት ለልማት የምንተጋበት አርማ ነው

አሶሳ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦  ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መገለጫና በአንድነት ለልማት የምንተጋበት አርማ ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አስካለች አልቦሮ ገለጹ።

በክልሉ 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።


 

በዕለቱም ንግግር ያደረጉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አስካለች አልቦሮ፤ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሲከበር የሰንደቅ ዓላማን ጥልቅ መልዕክት በመረዳት ለሀገር ያለንን ፍቅር የምናድስበት ነው ብለዋል።

ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መገለጫና በአንድነት ለልማት የምንተጋበት አርማ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መገለጫ ምልክት ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሀገራዊ ዕድገትን ለማቀላጠፍ የተግባር አንድነት የሚያሳዩበት እንደሆነ ገልጸዋል።

የሰንደቅ ዓላማን ክብር የምናሳየው ድህነትንና ኋላቀርነትን በመታገል ለኢትዮጵያ ከፍታ በአንድነት በመስራት ነው ሲሉም አክለዋል።

በዕለቱም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የፀጥታ አካላት እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም