ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ፍትሃዊ የባህር በር የማግኘት እና የመጠቀም መብቷን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ፍትሃዊ የባህር በር የማግኘት እና የመጠቀም መብቷን ለማረጋገጥ እየሰራች እንደትምገኝ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በተገኙበት ተከብሯል።


 

“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” ቀኑ የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የእድገት ጉዞዋን የተቃናና ስኬታማ እንዲሆን እየሰራች ትገኛለች።

የዚህ ቀጥተኛ መንገድ ማሳያ የኢትዮጵያ ባህር በር የማግኘት ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አካሄድ በቀጣናው የጋራ ትብብር እና ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ፍትሃዊ የባህር በር የማግኘት እና የመጠቀም መብትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

መንገዱም በሰላማዊ፣ በዲፕሎማሲያዊና በሰጥቶ መቀበል መርህ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም