ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ዓመቱን በሽንፈት ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ዓመቱን በሽንፈት ጀምሯል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 ረትቷል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሄኖክ ኤርሚያስ በ43ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሲዳማ ቡና ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን በሽንፈት ጀምሯል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታው ሶስት ነጥብ አሳክቷል።
በሁለተኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና ከአዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ኢትዮጵያ መድን ጋሞ ጨንቻን 2 ለ 0 አሸንፏል።
መቻል ሃዋሳ ከተማን፣ ሸገር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን እና ባህር ዳር ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ አንደኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።