ቀጥታ፡

ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማ እና መቻል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2019 (ኢዜአ)፦ በ1ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሸገር ከተማ፣ ባህር ዳር ከተማ እና መቻል ተጋጣሚዎቻቸውን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ውጤት አሸንፈዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ኢትዮጵያ ቡና እና ሸገር ከተማን ባገናኘው ጨዋታ ሸገር ከተማ 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የሸገር ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ካሌብ በየነ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በአብዬ ኤርሳሞ ስታዲየም በተከናወነው የሀድያ ሆሳዕና እና ባህር ዳር ከተማ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን 1 ለ 0 ረቷል፡፡

የባህር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግብ አንተነህ ተፈራ አስቆጥሯል፡፡

በሌላ ጨዋታ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መቻል በቢንያም ተክሉ ብቸኛ ግብ ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም