የመደመር መንግሥት ሁሉንም አቅሞች በማሰባሰብ የሕዝብን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የመደመር መንግሥት ሁሉንም አቅሞች በማሰባሰብ የሕዝብን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 1/2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግሥት ሁሉንም አቅሞች በማሰባሰብ የሕዝብን የላቀና ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ ይህንን ያሉት ዛሬ ማለዳ ከከተማው ምክር ቤት አባላትና ከነዋሪዎች ጋር በመሆን ባደረጉት የማህበረሰብ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወቅት ነው።
ሙሉ ጤንነቱ የተጠበቀና አምራች ትውልድ ለመገንባት በከተማዋ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ገልጸዋል።
የከተማው ነዋሪ እነዚህን መሰረተ ልማቶች ዘወትር በአግባቡና በባለቤትነት ሊጠቀምባቸው እንደሚገባ መክረዋል።
በዘርፉ የሚደረጉ ጥረቶችና የሚሰሩ ሥራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ የሚያስቆም ምንም ዓይነት ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ተናግረዋል።
የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ የከተማችንን ዘላቂ ልማትና ሰላም ለማስጠበቅ ሁሉም ሰው በጋራና በትብብር መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።