ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ማምሻውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሪያን ምቤሞ በ73ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ ዩናይትድ መሪ ሆኗል።
ዶምኒክ ሶላንኪ በ92ኛው ደቂቃ ስፐርስን አቻ አድርጓል።
የቶተንሃሙ አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር በ78ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
በመጀመሪያው አጋማሽ ስፐርስ፣ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ዩናይትድ ብልጫ ነበራቸው።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በስድስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ከድል ርቋል።
ቶተንሃም በበኩሉ በሶስት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ሲሆን በውጤት ማጣት ጉዞው ቀጥሏል።