ቼልሲ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ ወደ አሸናፊነት የተመለሰበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።
በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ቼልሲ ቦርንማውዝን 5 ለ 1 ረትቷል።
ጆአኦ ፔድሮ እና ጆርዳን ሄንደርሰን በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥሩ ሞርጋን ሮጀርስ ቀሪዋን ጎል ለሰማያዊዎቹ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ኢቫቢልሰን የቦርንማውዝን የማስተዛዘኛ ግብ አስቆጥሯል።
ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ቼልሲ በ10 ነጥብ ደረጃውን ከ10ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉም ሶስተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦርንማውዝ በሶስት ነጥብ ከነበረበት 17ኛ ደረጃ ወደ 18ኛ ዝቅ በማለት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ገብቷል።
ቦርንማውዝ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ብራይተን ሰንደርላንድን 2 ለ 0፣ ኤፕስዊች ታውን ፉልሃምን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
አስቶንቪላ ከብሬንትፎርድ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።