ቀጥታ፡

ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ጨዋታው በሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ተካሄዷል።

ሁለቱ ቡድኖች በውድድሩ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አሳክተዋል።

ዛሬ አስቀድሞ በተካሄደ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ነገሌ አርሲ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም