ቀጥታ፡

አትሌት መስከረም ማሞ በሊዝበን ማራቶን አሸነፈች

አዲስ አበባ፤መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፦39ኛው የሊዝበን ማራቶን ዛሬ ተካሄዷል፡፡

በሴቶች አትሌት መስከረም ማሞ 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ አሸንፋለች።

ጠጂቱ ስዩም እና በሻንኬ ኢሙሼ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣት የኢትዮጵያን የበላይነት አረጋግጠዋል።

በወንዶች ዩጋንዳዊው ማርቲን ናይቤይ ሙሳ አሸንፏል።

ኢትዮጵያዊው አትሌት ደሳለኝ ይሌ አራተኛ ወጥቷል።

አብዲ ዓሊ ሰባተኛ እና ደምሱ ገመዳ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

የሊዝበን ማራቶን ከእ.አ.አ 1986 አንስቶ እየተካሄደ የሚገኝ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ነው።

የማራቶን ውድድሩ እውቅ አትሌቶች ከሚሳተፉባቸው ውድድሮች መካከል ይጠቀሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም