ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ነገሌ አርሲ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ነገሌ አርሲ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2019(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ነገሌ አርሲ አንድ አቻ ተለያየተዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናትናኤል ዳንኤል በ52ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪ መሆን ችሎ ነበር።
ዳዊት ተፈራ በ63ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ነገሌ አርሲን አቻ አድርጓል።
ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያ ጨዋታቸውን አንድ ነጥብ አግኝተዋል።
በሁለተኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት የደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ነገሌ አርሲ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ጨዋታውን ያከናውናል።